የሀገር ውስጥ ዜና

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች የዘማች ሚሊሻ ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

By Melaku Gedif

November 29, 2021

በደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኙ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ለመሰብሰብ የዩኒቨርሲቲው  መምህራን እና ሠራተኞች ለአስራ አምስት ቀናት የሚቆይ የሰብል መሰብሰብ ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ የዩኒቨርሲቲው የምርምና ህትመት ዳይሬክተር እና የሰብል ማሰባሰብ ንቅናቄው አስተባባሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አስማማው ካሳሁን ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተነሳሽነት እንዲሁም የክልሉ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሰብል ማሰባሰብ ንቅናቄ መፈጠሩን የሚናገሩት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ÷  ንቅናቄው ከህልውና ዘመቻው ጋር ተያይዞ አገሪቱ የሚገጥማትን የምግብ ክፍተት ሊደፍን እንደሚችል አመላክተዋል።

ከስድስት መቶ በላይ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች እየሳተፉበት ያለው ይህ ንቅናቄ÷ በመጀመሪያ ቀን ብቻ የ125 ዘማች ሚሊሻ ቤተሰቦችን፥ ከ70 ሄክታር በላይ የተሸፈነ ሰብልን መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲተው ሶስት ዐቢይ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ስራዎችን እየሰራ እንደሚገገኝ ከኢፕድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!