አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት “ኦሚክሮን” የተሰኘውን አዲሱን የኮቪድ19 ቫይረስ ዝርያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሳየው የስርጭት ባህሪ አደገኛ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ቫይረሱ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ባህሪውን የሚቀያይርና በርካታ ሰዎችን እያጠቃ የሚገኝ ወረርሽኝም ነው ተብሏል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለ194 አባል አገራቱ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በአፋጣኝ የኮቪድ19 መከላከያ ክትባት እንዲያዳርሱ ማሳሰቡን የዘገበው ሲ ጂ ቲ ኤን ነው፡፡