አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሶስተኛ ጊዜ በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ አርብቶ አደሮችን ስርአተ ምግብ ለማሻሻል ያለመ የፓናል ውይይት በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡
በፓናል ውይይቱ ዓለም አቀፍና አገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅቶችን ጨምሮ በሶማሌ ክልል የሚገኙ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተሳተፉ ሲሆን፥ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ተመላክቷል ።