የሀገር ውስጥ ዜና

በአሜሪካ የኮሎራዶ የሪፐብሊካን ምክትል ሊቀመንበር የ #በቃ ንቅናቄን ተቀላቀሉ

By Meseret Awoke

November 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኮሎራዶ የሪፐብሊካን ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ፐርሲላ ራሀን የጆ ባይደን መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የያዘውን አቋም መቃወማቸውን አስታወቁ፡፡

ምክትል ሊቀመንበሯ ከኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪል ካውንስል ጋር በነበራቸው ስብሰባ ነው የጆ ባይደን መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የያዘውን አቋምና ድርጊቱን የተቹት፡፡

ኢትዮጵያውያን ያለጣልቃ ገብነት እንዲኖሩ መተው እንደሚገባ ያመለከቱት ፐርሲላ ራሀን ÷ ማዕቀቡን አስመልክተውም ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

ከኢትዮጵያውያን ጋር መሆናቸውን የ #በቃ ንቅናቄን ተቀላቅለው ማሳየታቸውን በትዊተር ገጻቸው አመልክተዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!