የሀገር ውስጥ ዜና

የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 4 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ወደ አገር ውስጥ ገብቷል- የንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን

By Feven Bishaw

December 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ህዳር 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ካቀደው 8 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ውስጥ በመጀመሪያ ዙር 4 ሚሊየን ኩንታል ማስገባቱን የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ

ተጨማሪ 4 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ በሚቀጥሉት 15 ቀናት ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አቻ ደምሴ የተናገሩ ሲሆን÷ ምርቱ በአዳማ ፣ ሻሸመኔ ፣ባህርዳር ፣ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ በሚገኙ የኮርፖሬሽኑ አምስት ማዕከላት እንደሚሰራጭ ገልጸዋል።