የሀገር ውስጥ ዜና

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጉብኝት ቤጂንግ ለኢትዮጵያ ያላትን አጋርነት በተግባር ያረጋገጠችበት ነው – ምሁራን

By Feven Bishaw

December 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ጉብኝት ቤጂንግ ለኢትዮጵያ መንግስት ያላትን አጋርነትና የጠበቀ ወዳጅነት ዳግም በተግባር ያረጋገጠችበት ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የዲፕሎማሲና የህግ ምሁራን፥ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ከተነሱ ሀይሎች ጎን ለቆሙ የምዕራቡ ዓለም መንግስታት ጠንካራ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ብለዋል።