የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ነው

By Meseret Awoke

December 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫና የሚቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

ሰልፉ በኢትዮጵያ ላይ የሚካሄደው ጣልቃ ገብነት ”ይብቃ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡

የዩኒቨርሲቲው አባላት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እና የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ የሚከናወነው መርሃ ግብር እንደተጠናቀቀ÷ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት በአሜሪካ ኤምባሲ በር ላይ በመገኘት ተቃውሟቸውን እንደሚያሰሙ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!