የሀገር ውስጥ ዜና

230 ሚሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት የወሊሶ ከተማ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ስራ ተጀመረ

By Meseret Awoke

December 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 230 ሚሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት የወሊሶ ከተማ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ስራ ተጀመረ።

ግንባታውን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ አስጀምረውታል።

ለፕሮጀክቱ ግንባታ 230 ሚሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን÷ ገንዘቡም ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር የተገኘ መሆኑም ተገልጿል።

የፕሮጀክቱን ግንባታ ‘ጂቲፒ’ የተሰኘ አገር በቀል ድርጅት የሚያካሄድ ሲሆን÷ ጂ ኢ ዲ ኤ ጂ የተባለ አማካሪ ድርጅትም የማማከሩን ስራ የሚሰራ መሆኑም ታውቋል።

ግንባታውም በ1 ዓመት ከ6 ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ መታሰቡንና ከ157ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!