የሀገር ውስጥ ዜና

በደብረሲና ከተማ በጸጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ አገልግሎቶች ስራ ጀመሩ

By Meseret Awoke

December 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረሲና ከተማ በጸጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ አገልግሎቶች ወደ ስራ ተመለሱ።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ወረራ በመፈጸም ንብረት ከማውደሙም በላይ የመብራት፣ የትራንስፖርትና መሰል መደበኛ አገልግሎቶች ተቋርጠው ነበር።

የሽብር ቡድኑ በመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ተቀጥቅጦ አካባቢው ነፃ ከሆነ በኋላ ህዝቡ ወደ መደበኛ ህይወቱ መመለሱን ኢዜአ ዘግቧል።

የከተማዋን የመብራት አገልግሎት ለማስጀመር የተቆራረጡ ገመዶች እየተጠገኑ ሲሆን ÷ ግብይት እና የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ነው።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!