የሀገር ውስጥ ዜና

የቤህነን ታጣቂ ቡድን መሪ ህድር መሐመድ አሊ በቁጥጥር ሥር ዋለ

By Feven Bishaw

December 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቤህነን ታጣቂ ቡድን መሪ የሆነው ህድር መሐመድ አሊ በአካባቢው ማኅበረሰብ ትብብር በቁጥጥር ሥር ዋለ።

የቡድኑ መሪ በክልሉ መንጌ ወረዳ ጎልሞሶ ቀበሌ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።

የታጣቂ ቡድኑ መሪ በቁጥጥር ሥር በዋለ ጊዜ 1 ክላሽ፣ 2 ካርታ፣ 60 የክላሽ ጥይት፣ 5 የጭስ ቦምብ፣ 1 ሞቶሮላ ሬዲዮ መገናኛ እና የሱዳን ወታደራዊ ልብስ አብሮ ተይዟል።