የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ሽብርተኛውን ህወሃት ማውገዛቸዉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

By Feven Bishaw

December 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ሽብርተኛውን ህወሃት ማዉገዛቸዉ የሚበረታታ እና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷በኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና ክብር ላይ ፈፅሞ እንደማይደራደሩ ድምፃቸውን ያሰሙት ነዋሪዎቹ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እየሰራ ላለው ጠንካራ ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ስራ ያላቸውን አጋርነት ገልፀዋል ብለዋል ።