አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚውል ከ45 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ17 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ እና የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ማከናወናቸዉን ከክፍለ ከተማዉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
የካ ክፍለ ከተማ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ15ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የስንቅ እና ልዩ ልዩ ድጋፎችን ማድረጉን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአዲስ አበባ ምክር ቤት ለመከላከያ ሰራዊት ከ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉንም እንዲሁ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ የቱሪዝም ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማትን በማስተባበር ለመከላከያ ሰራዊቱ የሰበሰበዉን ከ5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተገኝተዉ ማስረከባቸዉን ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም “እኔ አለሁ ለወገኔ” በሚል መሪ ሃሳብ የፋሲልና የባህርዳር ከነማ ስፖርት ደጋፊዎች ማህበራት በጋራ በመሆን ከሰሜንና ደቡብ ወሎ ተፈናቅለው ደብረብርሃን ከተማ ለሚገኙ ወገኖች ከ1ነጥብ 8ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የምግብ ግብዓት አስረክበዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!