የሀገር ውስጥ ዜና

በቤይሩት የ’በቃ’ ንቅናቄ ሰልፍ ተካሄደ

By Meseret Awoke

December 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ’በቃ’ ንቅናቄ አካል የሆነውና ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በሊባኖስ ቤይሩት ከተማ ተካሄደ።

‘እኔ የአባቶቼ ልጅ ነኝ’ በሚል መሪ ሀሳብ በቤይሩት ‘ዳውንታውን‘ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ እየተካሄደ ባለው ሰልፍ በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳትፈዋል።

ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሱ ውጫዊ ጫናዎች የሚቃወሙና “የራሳችንን ችግሮች በራሳችን እንፈታለን” የሚሉ ሀሳቦችን ያዘሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጁት በሊባኖስ የሚኖሩ ወጣት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!