የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አሸባሪው ህወሓት ከአክሱም በተመሳሳይ በላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ የፈጸመውን ተግባር አወገዙ

By Meseret Awoke

December 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከአክሱም በተመሳሳይ በላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ የፈጸመውን ተግባር ኮንነዋል፡፡

አምባሳደሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ሃሳብ ÷ አሸባሪው ቡድን የታሪካዊቷን አክሱም ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ መንደርደሪያን በማረስ መሰረተ ልማቱን ማውደሙን አንስተው ÷ ይህንን ተከትሎ የተለያዩ አካላት ተግባሩን ማውገዛቸውን አስታውሰዋል፡፡

ወራሪው ቡድን ላልይበላን ወርሮ ይዞ በነበረበት ወቅት ከአክሱም በተመሳሳይ የላልይበላን አውሮፕላን ማረፊያ መዝረፉንና ማውደሙን አንስተዋል፡፡

ይህም ቡድኑ ተወዳዳሪ የሌለው ወንጀለኛ እና ዘራፊ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!