አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ’በቃ’ ንቅናቄ አካል የሆነው አሜሪካና ሌሎች ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫናና ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት እየተካሄደ ይገኛል።
በሰልፉ ላይ በዋሺንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ-ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኢዜአ ከሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር የዋሽንግተን ዲሲ ገብረ ሃይል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን የተሳሳተ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ እስክታስተካክል ድረስ ሰልፉ በቋሚነት የሳምንቱ እሁድ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ መካሄድ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
የ’በቃ’ ንቅናቄ አካል የሆኑ ሰላማዊ ሰልፎች እስካሁን በሰሜን አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና አፍሪካ አህጉራት በሚገኙ በርካታ ከተሞች ተካሂደዋል።
የ’በቃ’ ንቅናቄ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ በሚካሄደው ሰልፍ ንቅናቄው ወደ ኦሺኒያ (አምስተኛው) አህጉር ይደርሳል።
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!