የሀገር ውስጥ ዜና

ለሸኔ ታጣቂ ሊተላለፍ የነበረ ከ 2 ሺህ በላይ የብሬን ጥይት  ዓለም  ገና ከተማ  ላይ ተያዘ

By Mekoya Hailemariam

December 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻን አዋሽ አርባ ባደረገ የቤት መኪና ውስጥ ተደብቆ ለሸኔ ታጣቂ ሊተላለፍ የነበረ 2 ሺህ 560 የብሬን ጥይት ተያዘ።

ጥይቱ ዓለም  ገና ከተማ  ላይ መያዙ ነው የተመለከተው።

ኅብረተሰቡ ያደረሰውን ጥቆማ መሠረት አድርጎ የኦሮሚያ ፖሊስ ባደረገው ክትትል የብሬን ጥይቱ ተይዟል።