የሀገር ውስጥ ዜና

መቱ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሠራዊት ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

By Alemayehu Geremew

December 09, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መቱ ዩኒቨርሲቲ በጦር ግንባር እየተፋለመ እና የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከምሁራን እና ከሠራተኞቹ ጋር ውይይት ማካሄዱም ነው የተገለጸው።

በውይይቱ ማጠቃለያም ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ለሀገራቸው የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራ ጎን ለጎን የአካባቢውን ማኅበረሰብ ለመጥቀም እየሰራ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፥ ሀገር ላይ በተፈጸመው ወረራ የሚጠበቅበትን መወጣቱን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡