አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሰንጋዎች፣ እሽግ ውሀዎች፣ የደረቅ ምግቦችና የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለመከላከያ ሠራዊት በወሎና በሃርቡ ግንባር በመገኘት ድጋፍ አድርጓል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት “የአሸናፊነት የምድር ድሮኖች” መሆናቸውን ገልጸው፥ የህወሓት የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ አይነተኛ ሚና መጫወታቸውን ገልጸዋል።