የሀገር ውስጥ ዜና

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫና በመቃወም ሰልፍ አደረጉ

By Feven Bishaw

December 10, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው እንዲሁም በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫና በመቃወም ሰልፍ አደረጉ።

ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ ገደብ የለሽ ጫና እና የሃሰት ፕሮፖጋንዳዎችን ተቃውመዋል።