አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ባለሃብቶች ጥምረት ለአገሩ ህልውና ከልጁ ጋር በክብር ለተሰዋው የአቶ እሸቴ ሞገስ ቤተሰቦች 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉን የአቶ እሸቴ ሞገስ ታናሽ ወንድም ዶክተር ይተብቱ ሞገስ ተረክበዋል፡፡
አቶ እሸቴ ሞገስ ከልጃቸው ይታገስ እሸቴ ጋር በመሆን በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን የአሸባሪው ህወሃት ዘጠኝ ወራሪ ኃይሎችን በጀግንነት በመግደል በክብር መሰዋታቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ትናንት የክልል መንግሥት ለሕዝብና ለአገራቸው ክብር መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን ቤተሰቦች በመንከባከብና በማገዝ አደራውን እንደሚቀበል በይፋ መግለፃቸው ይታወቃል፡፡