የሀገር ውስጥ ዜና

የሽብር ቡድኑ በወረራቸው አካባቢዎች ላይ ያደረሰው ጉዳት ግቡ ኢትዮጵያን ማፍረስ መሆኑን ያሳያል-ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

By Feven Bishaw

December 12, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች ህወሓት በፈፀመው ወራረ ምክንያት የወደሙ የመንግስትና የግል ተቋማትን ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ የህወሓት የሽብር ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች የፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊትና በህዝቡ መሰረታዊ ጥቅሞች ላይ ያደረሰው ጉዳት የሽብር ቡድኑ አልፋና ኦሜጋ ግቡ ኢትዮጵያን ማፍረስ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡