የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመዲናዋ ህዝባዊ ሰራዊት ምስጋና አቀረቡ

By Feven Bishaw

December 12, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመገኘት ምሽቱን አከባቢያቸውን የሚጠብቁ ነዋሪዎችን ስራ ጎብኝተዋል።

በምሽቱ ጉብኝት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ነፃነት ዳባ እንዲሁም ሌሎች የከተማና የክፍለ ከተማው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡