የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ተማሪዎች እና መምህራን አገራዊ ጥሪውን በመቀበል ላደረጉት ንቁ ተሳትፎ ምስጋና አቀረቡ

By Meseret Awoke

December 13, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀገራዊ ዘመቻው ውጤታማነት ለአንድ ሳምንት መደበኛ ትምህርት ተዘግቶ ሲሰጥ የነበረው ማህበራዊ አገልግሎት ተጠናቀቀ፡፡

ለአንድ ሳምንት በቆየው የማህበራዊ አገልግሎት በመላው ኢትዮጵያ ተማሪዎች እና መምህራን የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብስብ ፣ ደም በመለገስ፣ ድጋፍ በማሰባሰብ እና ስንቅ በማዘጋጀት ተሳትፈዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ÷ ተማሪዎች እና መምህራን አገራዊ ጥሪውን በመቀበል ያደረጉትን ንቁ ተሳትፎ አድንቀው ÷ ለተሳትፏቸውም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘመቻው ለአገሩ እና ወገኑ የሚችለውን ለማድረግ የማይሰስት እና ኢትዮጵያን ወደፊት ለማሻገር ዝግጁ የሆነ ትውልድ መኖሩን ያሳየ ነው ሲሉም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በቀጣይም ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና እድገት ትምህርት ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ በትምህርት ገብታው ተመሳሳይ በሆነ አገራዊ ስሜትና ቁርጠኝነት ተግታችሁ እንደምትሰሩ ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉም ተናግረዋል።

ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ትምህርታቸውን መጀመራቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!