አዲስ አበባ፣ ታህሳስ4፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አሜሪካ የኢትዮጵያውያንን ድምፅ መስማት እና ከጎናቸው መቆም እንደሚገባት የእስራኤል የፓርላማ አባል እና የቀድሞ የደህንነት መስሪያ ቤት ምክትል ኃላፊጋዲ ይቫርከን ጠየቁ።
ጋዲ ይቫርከን ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቤተ እስራኤላውያንን በመወከል ደብዳቤ ጽፍዋል።
በደብዳቤያቸውም አሜሪካ ሕጋዊውን የኢትዮጵያ መንግሥት እንድትደግፍ ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ ቀደምት አገራችን ናት ያሉት ጋዲ ይቫርከን በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው በመጥቀስ ሰላም እንዲወርድ እንፀልያለን ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰላምና ፀጥታ መጠበቅ የቤተ እስራኤላውያን ማህበረሰብ ሰላምና ፀጥታ መጠበቅ መሆኑን በፃፉት ደብዳቤ ገልፀዋል፡፡
በጦርነት የወደሙ ንብረቶች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ እንደሚያሳስባቸው ገልጸው፥ ግጭቱን ለመፍታት፣ የተፈናቀሉ ዜጎቹን መልሶ ለማቋቋምና ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል፡፡
አሜሪካም ይህ ጦርነት እንዲቆም ግልጽ መልክዕት ለህወሓት ማስተላለፍ እና በቡድኑ ላይ ጫና ማሳደር እንዳለባትም አጽንኦት ሰጥተዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!