የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ ሚ ዐቢይ ለዳያስፖራው ያቀረቡት ጥሪ የኢትዮጵያን ገጽታ የሚቀይር ነው – ምሁራን

By Feven Bishaw

December 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዳያስፖራው ወደ አገር ቤት እንዲገባ ያቀረቡት ጥሪ የኢትዮጵያን ገጽታ የሚቀይር ምቹ አጋጣሚ በመሆኑ ፈጣን ምላሽ መስጠት ይገባል ሲሉ በጀርመንና በአየርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ተናገሩ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በበይነ መረብ ቆይታ ያደረጉት በጀርመን የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ዶክተር ጸጋዬ ደግነህ፥ በዚህ ወሳኝ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 1 ሚሊየን ዜጎች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ጥሪ ማቅረባቸው በውጭ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለአገሩ ያለውን ፍቅር የሚያሳይበት ምቹ አጋጣሚን የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል ።