የሀገር ውስጥ ዜና

ኢንስቲትዩቱ በምርምር ያገኘውን ዘመናዊ የሰብል መፈልፈያ ማሽን አስተዋወቀ

By Feven Bishaw

December 15, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኦሮሚያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በምርምር ያገኘውን ዘመናዊ የበቆሎና ሌሎች ሰብሎች መፈልፈያ ማሽን አስተዋውቋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በጅማ ዞን ቀርሳ ወረዳ ማሽኑን ያስተዋወቀ ሲሆን፥ በቀጣይ በቆሎ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ለማስፋፋት እንደሚሰራ አስታውቋል።