የሀገር ውስጥ ዜና

የአሸባሪ ቡድኑን እኩይ ተግባር የሚያወግዙ ሰልፎች በሀረር፣ ደብረማርቆስ፣ ዲላና ሳውላ፣ ጋምቤላና አሶሳ ከተሞች ተካሄዱ

By Feven Bishaw

December 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪ ቡድኑን ህወሃት እኩይ ተግባር የሚያወግዙ እና አሜሪካና አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዙ ሰልፎች በሀረር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ዲላና ፣ ሳውላ፣ ጋምቤላ እና አሶሳ ከተሞች ተካሄዱ፡፡

የሀረሪ ክልል ሴቶች አሸባሪው ህወሓት በወረራ ይዞቸው በነበሩ አካባቢዎች በሴቶች እና ህፃናት ላይ ያደረሰውን ጥቃት በማውገዝ “ለእህቴ ጠበቃ ነኝ፤ ልጄ ጥቃት ሲደርስባት ዝም አልልም፤ መሪዬ ሲዘምት ለኢትዮጵያ እኔ አለሁላት” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሴቶችና ህፃናትን መድፈሩ እንዲሁም የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል ህፃናቱን ወደ ጦርነት መማገዱ እንዳስቆጣቸው የተናገሩት ሴት ሠልፈኞቹ፥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ቡድን እያደረሰ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት አይተው አንዳላየ ማለፋቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡