የሀገር ውስጥ ዜና

ቆጣሪ አንባቢ በመምሰል ቤት ለቤት በመዘዋወር ሲዘርፉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Meseret Awoke

December 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ከተማ የቆጣሪ አንባቢ በመምሰል ቤት ለቤት በመዘዋወር ሲዘርፉ የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጋምቤላ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ድርጊቱ የተፈፀመው በጋምቤላ ከተማ ኒው ላንድ ሰፈር ሲሆን ÷ ተጠርጣሪዎቹ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መያዛቸው ተመላክቷል፡፡

ህብረተሰቡ ቆጣሪ አንባቢዎች ለንባብ በሚመጡበት ወቅት የተቋሙን መለዮ ልብስ እና የተቋሙ ሰራተኛ መሆናቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ወይም ባጅ የያዙ መሆናቸውን ሳያረጋግጡ ወደቤታቸው ማስገባት እንደሌለባቸው አገልግሎቱ አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥፋትና ውድመት የሚያደርሱ እና መሰል ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ሲመለከት ለፀጥታ ኃይሎች ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ አገልግሎቱ መጠየቁን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!