አዲስ አበባ ፣ ታህሳሰ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኮትዲቭዋር የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ አንጎላ አቀኑ።
ፕሬዝዳንቷ በአንጎላ በሚኖራቸው ቆይታም ከፕሬዘዳንት ጆ ማኑዌል ሎሬንሶ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች እንዲሁም የኢትዮጲያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አንጎላ በደቡብ ምእራብ አፍሪካ ሀገራት መካከል በአፍሪካ ህብረት ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።
እ.ኤ.አ ከቅኝ ግዛት ነፃ ከወጣችበት ከ1970ዎቹ ጀምሮ የተጀመረው የኢትዮጵያ እና አንጎላ ግንኙነት በተለይም በፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ መስክ ጠንካራ መሆኑ ይነገርለታል።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአንጎላ በኋላ ወደ ጋቦን በማቅናት ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢቢሲ ዘግቧል።