አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከከፋፋይ ኃይሎች በተቃራኒው ተሰልፈን ከኢትዮጵያ ጋር በመቆም አሁን ያለው መንግሥት ለሀገሪቱ ሕዝቦች እና ለቀጣናው ሀገራት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያደርገውን ጥረት መደገፍ ይገባል ሲሉ የአሜሪካ ኮንግረስ አባሏ ሼይላ ጃክሰን ሊ ገለጹ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ጠንካራ የኢኮኖሚ ሞተር ነች ያሉት የኮንግረስ አባሏ፥ በከፋፋይ ሃይሎች ሴራ ሳንዘናጋ ከኢትዮጵያ ጋር በመቆም መንግስት ለሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያደርገውን ጥረት መደገፍ አለብን ብለዋል በቲዊተር ገጻቸው ላይ።