አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ለምግብ ዋስትና ችግር ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሆን ከ42 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተበርክቷል፡፡
ድጋፉ የአለም ምግብ ፕሮግራም በድርቅ ለተጎዱ የክልሉ አርብቶ አደሮች እንዲከፈል በተደረሰው ስምምነት መሰረት በኢትዮጵያ መድን ድርጅት፣ ኒያላ፣ ኦሮሚያና አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች አማካኝነት ክፍያው ተፈፅሟል ነው የተባለው፡፡