አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሠመራ፣ ሎጊያ፣ ዱብቲ፣ አይሳኢታ፣ ሚሌ፣ ዲችኦቶ፣ ኤሊዳኣር እና ጋላፊ ከተሞች ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
አሸባሪው የህውሃት ቡድን በአፋር ክልል ወረራ ባደረገበት ወቅት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ውድመት ማድረሱ የሚታወስ ሲሆን፥ በክልሉ ከኮምቦልቻ ሰብስቴሽን የሚያገኙት 7 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
ሆኖም የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብና የጥገና ሥራ ከትላንት ጀምሮ ከተሞቹ የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ማግኘታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡