የሀገር ውስጥ ዜና

በሀገራዊና የሀገረ መንግሥት ግንባታን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ምክክሮች እንደሚያስፈልጉ መንግስት በጽኑ ያምናል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

By Feven Bishaw

December 22, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋና ዋና ሀገራዊ እና የሀገረ መንግሥት ግንባታን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ምክክሮች እንደሚያስልጉ መንግሥት በጽኑ እንደሚያምን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ምክክሩ በአንድ ጊዜ ተጀምሮ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ፥ ምክክሩን ለማስጀመር ተቋማዊና ህጋዊ ማዕቀፎችን የማዘጋጀት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡