የሀገር ውስጥ ዜና

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

By Feven Bishaw

December 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው 1ኛ አመት 3ኛ መደበኛ የካቢኔ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል ።

በዚህም በከተማው የካሳና ምትክ ቦታ የሚሰጥበትና የልማት ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት ረቂቅ መመሪያ ላይ እንዲሁም የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤን ለማቋቋም በተዘጋጀ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል ።