አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በሊቀ መንበርነት የሚመሩትን ዓለም አቀፍ ኮሚሽን ወክለው በዱባይ አዘጋጅነት በሚካሄደው ትምህርት ላይ ያተኮረ የበይነ መረብ ውይይት ላይ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
በሪፖርታቸውም የፊታችንን በጋራ እንሠራለን የሚል ይዘት ያለው ትምህርት እና ማኅበረሰብ ላይ ያተኮረ ጽሁፍ በበይነ መረብ ማቅረባቸውን ከማኅበራዊ ትሥሥር ገፃቸው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ፕሬዚዳንቷ ሁላችንም የውይይቱ ተሳታፊዎች በትምህርት ላይ አካታች እና ዘላቂነት ያለው ተሃድሶ እና ለውጥ ለማምጣት የጋራ ራዕይ ይዘን የበኩላችንን ለመወጣት ቁልፍ ሚና አለን ብለዋል፡፡