የሀገር ውስጥ ዜና

በወገልጤና ከተማ የሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በሽብር ቡድኑ ህወሃት ሙሉ ለሙሉ ወድሟል

By Feven Bishaw

December 25, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደላንታ ወረዳ ወገልጤና ከተማ የሚገኘው መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በሽብር ቡድኑ ህወሃት ሙሉ ለሙሉ መውደሙ ተገለጸ።

በአካባቢው ለሚገኙ እስከ 600 ሺህ ለሚደርሱ ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጠው ሆስፒታሉ በአሸባሪው እና ዘራፊው ቡድን ተዘርፎ እና ወድሞ አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ደረጃ መድረሱ ተገልጿል፡፡