የሀገር ውስጥ ዜና

የዳያስፖራ አባላት በመዲናዋ ያለስጋት እንዲንቀሳቀሱ በቂ ዝግጅት ተደርጓል

By Feven Bishaw

December 25, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ወደ አገር ቤት የገቡ የዳያስፖራ አባላት በሚንቀሳቀሱባቸው ሥፍራዎች ሁሉ የጸጥታ እና ደህንነት ስጋት እንዳይገጥማቸው ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

‘የአንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደ አገር ቤት’ ጥሪ ተከትሎ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት በመግባት ላይ ናቸው።