የሀገር ውስጥ ዜና

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ለአፋር ክልል 7 ሚሊየን ብር የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

December 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በከፈተው ጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡

የክልሉ መንግስት ለአፋር ክልል ያደረገው ድጋፍ 5 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ደግሞ የዓይነት ነው፡፡

ድጋፉንም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን በአፋር ሰመራ ተገኝተው ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አሻድሊ ሃሰን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፥ የተደረገው ድጋፍ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስትና ህዝብ ለአፋር ክልል መንግስትና ሕዝብ ያላቸውን አብሮነት ለመግለጽ ያለመ ነው፡፡

በአፋር እና አማራ ክልሎች ገብቶ ወረራ የፈጸመውን አሸባሪውን የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊት በአፋርና አማራ ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻ፣ በተለያዩ ክልሎች ልዩ ኃይሎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያዊያን የተቀናጀ አንድነት ተከናንቧል ያሉት አቶ አሻድሊ፥ በዚህም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስትና ሕዝብ መሠል ድጋፎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ጨምሮ መላው ኢትዮጵያዊያን እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!