የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በሊቀ ጳጳስና የፀረ አፓርታይድ ታጋዩ ዴዝሞንድ ቱቱ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

By Meseret Awoke

December 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሊቀጳጳስና የፀረ አፓርታይድ ታጋዩ ዴዝሞንድ ቱቱ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

የደቡብ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስና የፀረ አፓርታይድ ታጋዩ ዴዝሞንድ ቱቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ዛሬ መገለፁ ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዴዝሞንድ ቱቱን የነፃነት ትግል ተምሳሌት ብለዋቸዋል።

ኢትዮጵያ በህልፈታቸው የተሰማትን ሀዘን ለደቡብ አፍሪካ ህዝብና መንግስት መግለፅ ትወዳለችም ብለዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን