የሀገር ውስጥ ዜና

ቦርዱ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ከፓርቲዎች ጋር እየመከረ ነው

By Feven Bishaw

December 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በፓለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ አቤቱታዎች ዙሪያ ከፓርቲዎች ጋር እየመከረ ይገኛል፡፡

በቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ በሚመራው በዚሁ ምክክር የፓለቲካ ፓርቲዎች በአባል እና አመራሮቻችን ላይ እንግልት እና እስር እየደረሰ ነው ሲሉ ያቀረቧቸውን አቤቱታዎች አጣሪ ቡድን በዝርዝር እየተመለከተ ነው።