አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ፋግታ ለኮማ ወረዳ በአሸዋ ቀበሌ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በ3 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።
አደጋው ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከቲሊሊ ወደ ባህር ዳር ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ዶልፊን ከዳንግላ ወደ አዲስ ቅዳም ሲጓዝ ከነበረ የጭነት አይሱዚ መኪና ጋር በመጋጨቱ የደረሰ ነው፡፡