አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ሀገር ቤት ለሚገቡ 1 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በልዩ ሁኔታ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እና የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ የ1 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተደረገውን ጥሪ ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት ለሚገቡ እንግዶች በልዩ ሁኔታ ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተሰሩ ባሉ ሁኔታዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ከአውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን መሰረት ማድረግ አለበት የተባለ ሲሆን፥ ማጭበርበርና እንግዶችን ማደናገር እንዳይኖር የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ህጉን ተከትለው ሊሰሩ እንደሚገባ ተነግሯል።
እንግዶች ቆይታቸውን እንዲያራዝሙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ስለሀገራቸው የተሟላ ገጽታ እንዲኖራቸው መረጃ የመስጠትና ማህበራዊ መስተጋብርን ማጠናከር አለባቸው መባሉንም ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!