የሀገር ውስጥ ዜና

ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ስንዴን በመስኖ ለማልማት ግብ ተጥሎ እየተሰራ ነው-ግብርና ሚኒስቴር

By Feven Bishaw

December 30, 2021

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2014(ኤፍ ቢሲ) በበጋ የመስኖ ልማት ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ስንዴን በመስኖ ለማልማት ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መለስ መኮንን እንደገለጹት፥ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ በበጋ ወቅት ስንዴን በመስኖ በማምረት ተሰፋ ሰጪ ለውጦች የተመዘገቡ በመሆኑ በቀጣይ ይህን አጠናክረን በማስቀጠል በያዝነው የምርት ዘመን ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የመስኖ ስንዴ በማልማት ከ16 ሚሊየን ኩንታል በላይ ለማምረት ግብ ተጥሎ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡