ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና በአምስት አሜሪካውያን ላይ አጸፋዊ ማዕቀብ ለመጣል ወሰነች

By Alemayehu Geremew

December 30, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በአምስት አሜሪካውያን ላይ አጸፋዊ ማዕቀብ ለመጣል መወሰኗን የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን ገለጹ፡፡

ቃል አቀባዩ የአሁኑ የቻይና ማዕቀብ አሜሪካ በሐምሌ ወር በቻይና ባለሥልጣናት ላይ ለጣለችው ማዕቀብ ምላሽ መሆኑን አስታውቀዋል።

አሜሪካ የቻይና ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ የጣለችው ከሆንግ ኮንግ አስተዳደር ጋር በተያያዘ ተፈጽሟል ባለችው ፖለቲካዊ ሴራ ውስጥ ተሳትፋችኋል በሚል መሆኑን ም አስታውሰዋል፡፡

ቻይና አሜሪካን ከዚህ በኋላ በውስጥ ጉዳያችን እንዳትገቢ ስትል ማስጠንቀቋም የሚታወስ ነው።

ጣልቃ የምትገባ ከሆነ ግን ጥቅምና ክብሯን ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች ሲል ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።