አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህወሓት የሽብር ቡድን ወረራ ምክንያት በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች ከሁለት ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት በድጋሚ ተጀምሯል።
በሁለቱም ከተሞች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ መደበኛ ትምህርት ተጀምሯል።
የሀይቅ ከተማ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ያሬድ ጌታቸው፥ በአሸባሪው ህውሓት ወረራ ምክንያት ሁለት ወር ከ15 ቀን በኃላ በድጋሜ ትምህርት መጀመሩን ገልፀዋል።
ትምህርት ቤቶቹም ባለው ግብዓት መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደትን እያስቀጠሉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችም በትምህርት ቤቶች ተገኝተው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!