አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑ ህወሓት በቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታልን ያደረሰውን ከባድ ኪሳራ ዳያስፖራዎች በአካል ተገኘተው ተመልክተዋል ፡፡
በዚህ ወቅትም የሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ ህክምናን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጠው ሆስፒታሉ በሽብር ቡድኑ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ቡድኑ በውድ ዋጋ የተገዙ ዋና ዋና የህክምና መሳሪያዎችን በሙያ የታገዘ ዘረፋ መፈጸሙ ነው የተገለጸው፡፡
ሆስፒታሉን መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ ያለውን ስራ በተመለከተም ለዳያስፖራዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!