የሀገር ውስጥ ዜና

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የስራ አፈጻጸም ግምገማ መታረም ያለባቸውን ጉዳዮች መለየት አስችሏል-ጠ/ሚ ዐቢይ

By Feven Bishaw

January 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የስራ አፈጻጸምን አስመልክቶ የተካሄደው ግምገማ መታረም፣ መጽናት እና መላቅ ያለባቸውን ጉዳዮች መለየት ማስቻሉን ተናገሩ።

በፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የስራ አፈጻጸምን አስመልክቶ የተካሄደው የሁለት ቀናት ግምገማ ዛሬ ተጠናቋል።