አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያ የታደለች ሀገር ናት፤ እጅግ ያስደሰተኝ የበዓል አከባበር ነው” ሲትል በላልይበላ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓልን የታደመች ጀርመናዊት ገለጸች።
ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የውጭ ዜጎች በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላል ይበላ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል እያከበሩ ነው።
አሚኮ ያነጋገራት ባርዞሎማአስ ማንፊርድ የመጣችሁ ከጀርመን ነው፤ በላል ይበላ ከባለቤቷ ጋር ተገኝታ በዓልን ማክበሯ እጅግ እንዳስደሰታት ተናግራለች።
ኢትዮጵያ የታደለች ሀገር ናት ፤ ኢትዮጵያ እንደሚባለው ሳትሆን ሰላም፣ ሕዝቦቿ እንግዳ ተቀባይ ናቸው ማለቷን አሚኮ ዘግቧል።
በቀጣይም ሌሎች የሀገሯ ዜጎች ኢትዮጵያን መጥተው እንዲጎበኙ እንደምታደርግ ገልጻለች።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!