አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ከዲሲ እና ከካናዳ ወደ ሀገር ቤት የገቡ ተጓዦች 30 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርገዋል።
ማለዳውን ከዲሲ የመጡ ኢትዮጵያዊያን በጉዟቸው ወቅት ያሰባሰቡትን 22 ሺህ ዶላር እና ከካናዳ ቶሮንቶ በተመሳሳይ ሁኔታ ያዋጡትን 8 ሺህ ዶላር ነው ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው የአይዞን ኢትዮጵያ አካውንት ገቢ ያደረጉት።
በተጨማሪም ወደ ሃገር ቤት የገቡት እንግዶች ይዘው የመጡትን የውጭ ምንዛሪ በባንክ በመመንዘር የሀገራቸው ጊዜያዊ ችግር ለመቅረፍ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በቆንጅት ዘውዴ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!