የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በነገው ዕለት ሊካሄድ የነበረው የ “በቃ” ሰልፍ ለቀጣይ ሳምንት ተላለፈ

By Feven Bishaw

January 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በነገው ዕለት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የ “በቃ” ወይም #Nomore ሰልፍ በዳያስፖራው ጥያቄ መሰረት ለቀጣይ ሳምንት መተላለፉ ተገለፀ፡፡

በርካታ የዳያስፖራው ማህበረሰብ አሁንም ወደ አገሩ እየገባ በመሆኑ ሰልፉ ቀጣይ ሳምንት የሚካሄድ መሆኑን ነው ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላከተው፡፡